ታማኝ ምንጮቻችን እንደገለፁት
የስርአቱ ደህንነት፤ ፖሊስ ሰራዊትና ካድሬዎች ከዚህ በፊት በአገር መከላከያ ሰራዊት ሲያገለግሉ ለቆዩትና በተለያዩ ጊዝያት ከውትድርና
ስራ የለቀቁ ወታደሮች ችግራቸውን አስመልክተው ተሰባስበው እንዳይነጋገሩ፤ ተደራጅተው እንዳይቃወሙና ህዝቡን እንዳያነሳሱ በመስጋት
ወደ ትውልድ ቦታችሁ ሂዱ በማለት እያባረሯቸው እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
መረጃው በማስከተልም እነዚህ የቀድሞ ወታደሮች በስልጣን ላይ ያለው ስርአት
ያለምንም የገንዘብ ድጋፍ ስላሰናበታቸው ትልቅ ስሜት ውስጥ ባሉበትና ስርአቱ በህዝቡ ላይ በሚፈፅመው ግፍ ተቃውሟቸው በሚገልፁበት
ባሁኑ ግዜ በተለይ መጪውን 2007 ዓ/ም በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ላይ እንዳያደናቅፉት በመስጋት የመበተኑ እርምጃ እየተካሄደ
መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።