በመቐለ፤ አክሱም፤ አዲግራት’ና
ሌሎች ቦታዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ውስጥ እየተማሩ ያሉት ተማሪዎች እንደገለፁት በተቋማችን ውስጥ የሚገኙ አስተማሪዎች
እውቀት እንድናገኝ ብለው ተገቢ ጥረት ስለማያደርጉ፤ በቂ መፅሕፍትና ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ መሳርያዎች ባለመኖራቸው አስፈላጊውን
እውቀት ማግኘት እንዳልቻሉና በዚህም ምክንያት በፈተና ወቅት ዝቅተኛ ውጤት እንድያመጡ ምክንያት እንደሆነ በዚህም ሳብያ በአስተማሪዎቹና
በተማሪዎቹ መሃል ያለመስማማት መፈጠሩ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተመሪዎቹ እንደገለፁት የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች
ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡትን ብዛት ያላቸው ተማሪዎች በሚድያ ላይ መግለፃቸው ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም
ሲሉ መናገራቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።