Friday, July 25, 2014

የአሸባሪነት ትርጉምና የወያኔ ኢህአዴግ አመለካከት!!



ሽብርና አሸባሪነት በተመለከተ ከአመታት በፊት ጀምሮ ብዙ እየተነገርለትና እየተፃፈለት መቆየቱና ሁኔታውን በማስመልከት የተለያዩ ትርጉሞች እየተሰጠው አሁን እስካለንበት ደረጃ መድረሱ ይታወቃል፣፣
 የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ባለ ስልጣናት አሸባሪዎችን አስመልክቶ ከራሳቸው ጥቅምና ፖለቲካዊ ይዘት እያስተሳሰሩ እውነትነት በሌለው መንገድ በግለሰቦች ቀጥታዊ አመራር  በንፁሃን ህዝቦች ላይ ግፍ ተፈፅመዋል እያሉ ነገር ግን እነዛ ግፍ ፈፅመዋል የተባሉትን ግለ-ሰቦች በቁጥጥር ስር ከገቡ በኋላ በላያቸው ላይ የሚደርሰውን ኢ-ሰብአዊ በደል የሰላም ሃዋርያና የዴሞክራሲ ተምሳሌት እንደሆኑ አድርጎው ራሳቸውን ከሚገልፁት ወያኔዎች ነጋ ጠባ ከሚገልፁት ቃል በሚፃረር መንገድ ሆን ብለው በጭፍን እየወነጀሉ በንፁሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ በደል ሲያደርሱ ይታያሉ።
  ባገራችን ለአሸባሪነት አስመልክቶ የሚሰጡ ጭብጦች በተለይ ገዢው መንግስት ተቆጣጥሮት ያለውን ስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል በጭቁኑ ህዝብ ላይ የሚያካሂደው ፀረ ዴሞክራሲያዊ ተግባሮች ተቀባይነት ስለሚያሳጣው ይህንን ተጠቅመው በተለያዩ ሚድያዎች ስርአቱን ለማጋለጥ በሚሞኩሩ የመፅሄትና የጋዜጣ አዘጋጆች፤ ህዝቡን በመምራት ፀረ መንግስት ተቃውሞ ለሚያካሂዱ ዜጎች፤ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጠቅመው ለሚታገሉ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችና አባላት ወ.ዘ.ተ አነሳሾች፤ ፀረ ልማትና ተላላኪዎች በሚል ስም እየፈረጁ በላያቸው ላይ ከፍተኛ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አፈና፤ እስርና ግድያ ሲፈፀምባቸው ማየት የተለመደ ተግባር ነው።
  ካለፉት አመታት ጀምሮ በማነሳሳት፤ ሽብር ፈጣሪነትና ፀረ ልማት ተብለው በወያኔ ኢህአዴግ እስር ቤት ገብተው እየማቀቁ የሚገኙ የህዝብ ወገን የሆኑ አርበኞች ማለት- ቀደም ሲል እንደነ ርእዮት አለሙ፤ ውብሸት ታየ፤ አንድዋለም አራጌ፤ መሃመድ አቡበከር፤ እስክንድር ነጋ፤ ናትናኤል ፈለቀ፤ ዘለአለም ክብረትና ሌሎች በርካታ አርበኞች፤ ባለፉት ሳምንትም ቢሆን-እንደነ የግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ  እንዳርጋቸው ፅጌ  የሸዋስ ከበደ፤ ስለሺ አያሌው፤ አብርሃ ደስታና ሌሎች ስማቸው ያለተገለፁ የህዝቡን አላማ አንግበው በመታገል ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ለስቃይና ለመከራ እንዲጋለጡ መደረጋቸው መላው ያገራችን ህዝብ ያውቀዋል፣፣
 የወያኔ ኢህአዴግ መሪዎች አስመሳይነት መጨረሻ እንደሌለው ህዝባችን በሚገባ የሚያውቀው ቢሆንም በ2007 ዓ/ም እንዲካሄድ እየታሰበ ያለውን የስርአቱ የይስሙላ ምርጫ እንደተለመደው ኢህአዴግ ለብቻው ተወዳድሮ አሸነፍኩ ለማለትና አፋኝ ተግባሩ ገሃድ ለማድረግ ሆን ብሎ ምርጫ በሚቀራረብበት ሰአት ተሰሚነት ያላቸውና የህዝቡ ወገን ለሆኑ ግለሰቦች ፍፁም ታማኝነት በሌለው መንገድ በፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ሃይል እየፈረጀ ወደ እስር ቤት እየወረወራቸው ይገኛል፣፣
ሻማ ለራስዋ እየቀለጠች ብርሃንዋን ትለግሳለች እንደሚባለው በወያኔ እስር እየወደቁ የሚገኙ በርካታ ጀግኖች ታጋዮች ለሀገር ክብርና ለህዝብ ነጻነት ብለው እየተንቀሳቀሱ በነበሩበት ግዜ በስርአቱ እጅ ወድቀው ግፍና ስቃይ ቢደርሳቸውም እነሱ ያፈሯቸው የቁርጥ ቀን አርበኞች አሉና አሁንም የንሱን አላማና ቃል ተሸክመው የተነሱለትን አላማ ዳሩ ላይ ለማድረስ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት ፍፁም የሚያጠራጥር አይደለም፣፣