Monday, October 13, 2014

በኢ,ህ.አ.ዴ.ግ መከላከያ ሰራዊት ከሃይል መሪ እስከ ክፍለ ጦር አዛዥ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ ውጥረት በተሞላበት መንገድ ጥያቄዎች መነሳታቸው ተገለፀ፣





ከመከላከያ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛ አዛዦች ከሚቀርቡ ሃሳቦች የወታደር ደመወዝ ጭማሪ እንዴት ብሎ ችግር እንደፈጠረና ሰራዊት እየጠፋ እንደሆነ፥ ግብፅ የአባይን ግድብ መገደብ ተቀብየዋለሁ ብትልም፤ ቆይታ ችግር ልትፈጥር ስለምትችል በውስጣችን ያለው ሰራዊትም እየጠፋ ስለሆነ እንዴት አድርገን እናስቁመው የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች እንደተነሱ ለማወቅ ተችሏል፣
 በታችኞች ወገን ደግሞ “እየጠፋ ያለው ሰራዊት ምክንያቱ እናንተና መንግስት የፈጠራችሁት ችግር ነው ይህም ለሰራዊቱ ሳታማክሩ ደመወዙን ከላይ እየቆረጣችሁ ታስቀራላችሁ በተለይ በቅርቡ ለልብስ 480 ብር ለጫማ 330 ብር ለቲሸርትና ሌሎችም እየተባለ ይቀነሳል፣ ይህ ደግሞ መንግስት በሰራዊቱ ላይ ንግድ እያካሄደ ነው የተጨመረው ደመወዝም ተመልሶ ወደ መንግስት ገቢ እየተደረገ ነው፣” ሲሉ አማርረው ተናግረዋል፣
  እነዚህ የታችኞች የሰራዊቱ ሃላፊዎች ጨምረውም።- “የ7 አመት አገልግሎት ጨርሶ ኑሮየን ልምራ ብሎ የሚጠይቅ ወታደር ይከለከላል፣ መንግስት ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ እየጣሰው ነው ይህ ሁኔታ በእንዲህ ከቀጠለ በውትድርና የሚቀጥል ሰራዊት የለም እየጠፋ ወደ ሃገሩና ወደ ትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች እየተቀላቀለ ነው።” ሲሉ መናገራቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣