Friday, November 21, 2014

የኢህአዴግ ስርዓት መሪዎች የ7 ዓመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ የስራዊት አባላት። አሰናብቱን ለሚለው ጥያቄያቸው ወደ ጎን በመተው። እንደገና በኃይል አስገድደው እንዳስፈረሟቸው ተገለፀ፣




     የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት ባለፈው ወር በመከላከያ ደረጃ በተደረጉ ስብሰባዎች። የ7 ዓመት አገልግሎታችንን ስለጨረስን አሰናብቱን በማለት በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸውን የገለጸው መረጃው። የስርዓቱ ባለስልጣናት ግን ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ለሁለተኛ ግዜ አስገድደው ለ7 አመት እንዲቆዩ ማሰፈረማቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣
   ይህ በእንዲህ እያለ  ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱን የተቃወሙት የሰራዊቱ አባላት። ስለመብት ጉዳይ እያነሳችሁ  የምትናገሩት የት አለ በማለት። ከአመራሮቹ ጋር  ወደ አልተፈለገ ንትርክ ውስጥ መግባታቸውን መረጃው አክሎ አስታውቋል፣