Friday, November 21, 2014

የኢህአዴግ ገዢ ስርዓት። የበላይ ጀነራሎችን ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ሰበብ በመፍጠር እያባረራቸው እንደሆነ ተገለፀ፣




    ከመከላከያ ስታፍ ኣፈትልኮ በደረሰን መረጃ መሰረት። በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ የበላይ አመራሮች ሆነው ሲመሩ ከቆዩት አንዱ የሆነው ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ እንደሆነና። በአሁኑ ግዜ በሰራዊቱ አዛዦች ውስጥ ተፈጥሮ ባለው ችግር ምክንያት። ከስርአቱ ባለስልጣኖች ጋር ሊግባባ ባለመቻሉ። ሁሉም አይነት እንቅስቃሴህ ከኛ ጋር ሳትሆን ከተቃዋሚዎች ጋር ነው በማለት እንዳባረሩት ለማወቅ ተችሏል፣
    መረጃው ጨምሮ። በሰራዊቱ የበላይ አዛዦች ውስጥ የተደረገውን ፍሬ አልባ ተደጋጋሚ ስብሰባ። ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ከቦታው ተነስቶ የሱን ቦታ እንዲተኩ ከተባሉት አንዱ መሆኑ ሲነገር እንደቆየ የገለጸው መረጃው። በአሁኑ ጊዜ ግን ለአበባው ታደሰ ካለምንም የጡረታና ማቋቋሚያ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ ተሰጥቶት የነበረውን መኖርያ ቤት ሳይቀር መንጠቃቸውና። ላንተ ክብር ሳይሆን በሌላ መንገድ ነው የምናይህ ተብሎ መባረሩም። ለስራ ባለደርቦቹ ዱብዳ እንደሆነባቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል፣