Friday, November 21, 2014

በህዳሴ ግድብ ውስጥ በማህበር ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩ ወገኖች። የሰሩበትን ክፍያ የሚሰጣቸው አካል እንዳጡ የተገኘው መረጃ ገለፀ፣




    እነዚህ ከ 500 በላይ የሆኑ ሰራተኞች። ከግንቦት 2006 ዓ/ም ጀምረው ለ8 ወራት ያህል በማህበር ተደራጅተው ሲሰሩ ቢቆዩም። እንዲሰሩ ውል የገባላቸውን የመከላከያ ኩባንያ ተቋራጭ በገባላቸው ውል መሰረት ደመወዝ እንዲከፍላቸው ቢጠይቁም። አልከፍልም ማለቱን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣
    መረጃው በማስከተልም። በማህበር የተደራጁ ከ 500 በላይ የሆኑ ሰራተኞች። ከመጀመርያ ጀምረው አደራጅተው ሲመሯቸው የቆዩት ኮሎኔል ሙላውና ኮሎኔል ሃይለ ምላው የተባሉት መሆናቸውና። ስራ እንዲሰሩ በማለት ግድቡ ውስጥ ከሚሰራው የመከላከያ ኩባንያ  ኮንትራት ተስጥቷቸው እየሰሩ ቢቆዩም። የላባቸውን ዋጋ አልከፋላችሁም ስላላቸው። ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ ክስ ቢያቀርቡም። እስካሁን መፍትሄ ሳያገኙ ላይና ታች በማለት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣