Friday, November 21, 2014

በኢህአደግ የመከላከያ ሰራዊት ውሰጥ ያሉ አዛዦች። በሃገርና በህዝብ ሃብት ለስራ ማስኬጃ ተብሎ የቀረበላቸውን ንብረት እየሸጡ በሙስና ስራ ላይ መሰማራታቸውን። ከመከላከያ ውስጥ ምንጮቻችን አስታወቁ፣




      ባገኘነው መረጃ መሰረት። በማዕከላይ እዝ 8ኛ ክ/ጦር የመካናይዝድ አዛዥ የሆነው ብርጋዴር ጀነራል መሓመድ ብርሃን  ( ወዲ ጎጀላ )። ለስራ ተብሎ የተረከበውን አንድ የነዳጅ ማምላለሻ መኪና የጫነውን ሙሉ ነዳጅ ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በሚገኘው ጉዑሽ ክፍላይ በተባለው የነዳጅ ማደያ ሲሸጠው እንደተገኘ ተገለፀ፣
       በሙስና የተጨማለቀው ብርጋዴር ጀነራል መሃመድ ብርሃን የተባለው የስራዊት አዛዥ። በህዝቡ እንደተነቃበት ያወቁት የበላይ አዛዞቹ ለግዜው ከስራ አግደዉት እንዳለ የገለፀው ይህ መረጃ። ይህ የተደረገው ግን ለይስሙላ እንጂ በመከላከያ ስራዊት ባጀት ማጠፋፋት፤ የወታደሮች መሳሪያና ሌሎች እቃዎች መሸጥ የተለመደ ተግባር ቢሆንም። እስከ አሁን ግን ሙስናን የፈፀሙትና እየፈፀሙ ያሉት አዛዞች በላያቸው ላይ የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ ከመከላከያ ውስጥ ምንጮቻችን  ጨምረው አስረድተዋል፣