Friday, November 21, 2014

በአብይ-አዲ ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የአረናን ድርጅት ፓምፕሌት ለጥፋችኋል በማለት ህዝብ እያሰቃዩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣




   በአብይ-አዲ ከተማ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት። አረና የተባለው የተቃዋሚ ድርጅት ህዳር 2 /2007 ዓ/ም ህወሃት የሚከተለው የጥፋት መንገድ መሆኑን የሚያጋልጥ እንዲሁም  ህዝቡም በህብረት መቃወም እንዳለበትና በመጪው ምርጫም ህዝብ የፈለገውን መምረጥ እንደሚጠበቅበት የሚገልፅ ወረቀት እንደበተኑ የገለፀው መረጃው። በዚህ የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሬዎችም ህዳር 3/ 2007 ዓ/ም ወረቀት የበተኑ አባሎችን ለመያዝ  የታጠቁ ፖሊሶችን በማሰማራት ቤቶች እየተፈተሹ ሲሆን በተለይ አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ አሉላ ከተባለ ሆቴል አልጋ የተከራየ ግለሰብ ይዘው ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት አካባቢ በማውጣት ሲቀጠቅጡት እንደዋሉ ታውቋል፣
   ፀረ ህዝብ ፖሊሶች ሲደበድቡት  የታዘቡ ወገኖችም በሆቴሉ አልጋ ተከራይቶ መተኛት አይቻልም ወይ? ስለምን የሰው መብት ትገፋላችሁ? የሚሉና ሌሎችም ቢሆኑም። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ እንዳላገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣
     ከዚህ በኋላም የስርዓቱ ካድሬዎች ህዝብን ሰብስበው  በተቃዋሚዎች የሚጠራ ስብሰባ ማንም ሰው መውጣት እንደሌለበት፥ በቤቶቻቸው አካባቢም የሚበተን ይሁን የሚለጠፍ የተቃዋሚ ድርጅት ወረቀቶችን ሁሉም ሰው እየተከተለ መቅደድ እንዳለበት መምሪያ ያወረዱ መሆናቸው ተገልጿል፣