Friday, November 21, 2014

በዚህ ሳምንት አምባ-ገነኑን የኢህአዴግ መንግስት በመቃወም ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች። ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን/ ተቀላቀሉ፣




    ከትህዴን ማሰልጠኛ ማዕከል በደረሰን መረጃ መሰረት። በቅርብ ጊዜ ወደ ት.ህ.ዴ.ን ከተቀላቀሉ ወጣቶች ከፊሎቹን ለመጥቀስ፣-
-    ሀይሌ ገብረስላሴና ተስፋይ ካሕሳይ። ሁለቱም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን፤ ጉሎመኸዳ ወረዳ፤ ሸዊት ቀበሌ፤ በቕሎ ከተባለው ቦታ።
-    ክብሮም እንድርያስ። ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ደብረ ሓርማዝ ቀበሌ፤ እንዳካህናት ከተባለው ቦታ።
-    ሓዱሽ መብራህቶም። ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ማይ ወዲ- ዓንበራይ ቀበሌ፤ ዓዲ ጋባት አካባቢ።
-    ቴድሮስ ሸዊቶም። ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ-ኽልተ ቀበሌ፤ ዳብረ አካባቢ።
-    ተስፋይ ዳኘው። ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ዓዲ ሓንገለ ከተባለው አካባቢና ሌሎች የሚገኙባቸው ወጣቶች። ስርአቱን በመቃወም ወደ ትህዴን ተቀላቅለዋል፣
ወጣቶቹ ወደ ትህዴን ተቀላቅለው እንዲታገሉ ያስገደዳቸውን ምክንያት ሲገልፁ። ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የፈጠረው የመልካም አስተዳደር ችግር፤ ስራ አጥነትና ሌሎችም ፀረ ህዝብ አሰራር በሰፊው በመንሰራፋቱ ይህንን ለማስወገድም ስርዓቱ በሚያምንበት የትግል ስልት ከስልጣኑ ማስወገድ ብቻ ነው በማለት ወደ ትግል እንደመጡ ገልፀዋል፣