Sunday, January 4, 2015

የሽረ እንዳስላሴ ከተማ አስተዳደር በተቃዋሚ ድርጅቶች የሚካሄደውን ህዝባዊ ቅስቀሳ የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ በማሰናከል ስራ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ተገለፀ።



ምንጮቻችን ከሽረ ከተማ እንደገለፁት ሰላማዊ ትግል እያካሄደ ያለው የአረና ፓርቲ በመጭው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ከሽረ እንዳስላሴ ከተማ ህዝብ ጋር ለመወያየትና ቅስቀሳ ለማካሄድ ስብሰባ ለማድረግ በሚንቅቅሳቀስበት ሰዓት የከተማዋ አስተዳደር ለህዝብ እንድትሰበሰቡ ፍቃድ አልሰጠንም በማለት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከልክሎ እንዳባረራቸው ለማወቅ ተችሏል።
  መረጃው በማከልም የኢህአዴግ ጉጅሌ ስርዓት ግንቦት ወር 2007 ዓ.ም የሚካሄደውን አገራዊና ክልላዊ አስመሳይ ምርጫ ላይ ሰላማዊና ፍትሓዊ በሆነ መንገድ እንደሚካሄድ እየገለፀ ቢሆንም እንኳ በተግባር ግን የተቃዋሚ ድርጅት አማራሮችና አባሎችን ከህዝብ ጋር ተገናኝተው የቅስቀሳ ስራቸውን እንዳያሳልጡ እያሰናከላቸውና ህዝቡንም በተለያየ መንገድ በማስፈራራት ተቃዋሚዎች በሚያካሄዱት ሰብሰባዎች እንዳይሳተፉና ድጋፋቸውን እንዳይሰጧቸው  በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ አሁን በሽረ እንዳስላሴ ከተማ  አስተዳደር እየተፈፀመ  ያለው አሰራርም እየቀጠለ ያለ  የስርዓቱ እኩይ ተግባር መሆኑን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።