በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ
ያለውን የቤት ችግር እንዲያቃልሉ ተብለው የተሰሩት የኮንዶምኒየም ቤቶች አገልግሎት ሳይሰጡ እየተበላሹ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው የዚህ ምክንያትም ለመስሪያ ተብሎ የተበጀተውን
ገንዘብ የከተማው አስተዳዳሪዎች ከኮንትራክተሮች ጋር ተመሳጥረው ስለበሉት እንደሆነና ቤቱ ተሰጧቸው የገቡት ሰዎችም የተገነቡት ቤቶች
በጥራት ስላልተሰሩ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት ባለማግኘታቸው ምክንያት ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው አክሎም የከተማው አስተዳዳሪዎች ገንዘብ
ለማትረፍ ሲሉ የሰሩት ሽንት ቤት ጠባብና ለቆሻሻ ውሃ ማስወገጃ የሚሆን ቱቦ ስለሌለው በዚህ የተነሳም ተቆፍሯል የተባለው ጉድጓድ
ሞልቶ ወደ ጎዳናዎች በመደፋቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ለመጥፎ ሽታ ተጋልጠው እንደሚገኙ ገልፆ በተለይም ህፃናትና ሽማግሌዎች የተላላፊ
በሽታዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳሉ ሊታወቅ ተችሏል።
በዚህ የኮንዲሚኒየም ቤት የሚኖሩ ወገኖቻችን እያጋጠማችው ያለው ችግር እንዲፈታላቸው
በማለት ለሚመለከታቸው አካላት ካለፈው አመት ጀምረው ጥያቄ ቢያቀርቡም
ካድሬዎች ግን ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ከፈለጋችሁ እራሳችሁ በራሳችሁ ገንዘብ ማሰራት ትችላላችሁ እንጂ እኛ ምንም አይነት
መፍትሄ ልናደርግላችሁ አንችልም የሚል መልስ እንደመለሱላቸው መረጃው አመልክቷል።