Sunday, January 4, 2015

የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ በትግራይና በአማራ ክልል መካከል ያጋጠመውን መፍትሄ ያጣ ግጭት ጠንቁ የምዕራብ ትግራይ አስተዳዳሪዎች እንደሆኑ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ እንደጻፈላቸው ለማወቅ ተችሏል።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ በሁለቱ ክልሎች መካከል መሬትን በተመለከተ እያጋጠመ ባለው  ውዝግብ ምክንያት እየፈሰሰ ያለው ደም ወደ ሌላ ብጥብጥ መሄዱ እጅግ ስላስጨነቃቸው ወደ ምዕራብ ትግራይ ዋና አስተዳዳሪ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መፃፋቸውን ሊታወቅ ተችሏል።
   የደብዳቤው ይዘትም የምዕራብ ትግራይ ህዝብ ወደ መሬታችን እየመጡ ግጭት አስነስተው በህይወትና በንብረት ላይ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት በመሆናቸው ህዝባችሁንና መሬታችሁን ከየት እስከ የት እንደሆነ አውቃችሁ በተገቢው መንገድ ማስተዳደር አለባችሁ ከአሁን በኋላ ለሚነሳው ግጭት ተጠያቂዎች እናንተው ናችሁ ሲል የክልሉን መስተዳደር ወክሎ የፃፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መሆኑን ሊታወቅ ተችሏል።