Sunday, January 4, 2015

በኢ.ህ.አዴ.ግ እኩይ ስርዓት የተማረሩ የአርማጭሆ ተወላጆች በዳንሻ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።



በአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት የአርማጭሆ ተወላጆች በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት እኩይ ተግባር ተማርረው ታህሳስ 14/ ቀን 2007 ዓ/ም በርካታ ወገኖች በዳንሻ ከተማ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተገለጸ።
   እነኝህ ወገኖች የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሂዱ ያስገደዳቸው ዋና ምክንያትም መቶ አለቃ ሃይለማሪያም የተባለውን የቀድሞ ታጋይ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱት ከአርበኞች ጋር ትገናኛለህ ተብሎ ታፍኖ አድራሻው ከጠፋ አንድ አመት ያስቆጠረ ቢሆንም ህዝቡ ግን ወድየት አጠፋችሁት በህይወት ካለ ወደ ህግ ይቅረብ ወይ ደግሞ ይፈታልን በማለት ሃይለኛ ታቃውሞ እንዳካሄዱ የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ያሰጉኛል ያላቸውን ንፁሃን ዜጎች ባልዋሉበት ወንጀል ስማቸውን እያጠፋ ማሰርና መግደል የተለመደ ተግባሩ መሆኑን የታዘቡ የአይን እማኞች እየገለፁ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስርድቷል።