Wednesday, January 7, 2015

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ስራ ፈላጊዎች ስራ ለማግኘት የግድ በመጀመርያ የህወሃት አባላት ለመሆን እንደሚጠየቑ ተገለፀ።



   በአሁን ግዜ በትግራይ ክልል የሚገኘው የተማረ የሰው ሃይል የመንግስት ስራን አስመልክተው የሚወጡትን ማስታወቅያ አይተው ስራ እንዲቀጠሩ አስበው በሚሄዱበት ግዜ መጀመርያ የህወሃት አባል ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ወረቀት አምጡ አለበለዝያ በመንግስት ስራ ላይ ለመሰማራት እድል የላችሁም በመባል ስራ የማግኘት መብታቸውን ተከልክለው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አስታወቀ። 
   በዚሁ ፍትሃዊነት የጎደለው ተግባር የተቆጡ ስራ ፈላጊ ዜጎች በተለይ ቀደም ሲል በትግሉ ግዜ የነበሩ ወገኖች እንዴት የህወሃት መለያ ካርድ እምጡ ብላችሁ ትጠይቁናላችሁ እስካሁን ድረስ በድርጅቱ ውስጥ አልነበርንም ወይ? ብለው ቢናገሩም  የግድ ካርድ መያዝ አለባችሁ የሚል መልስ ስለተሰጠባቸው በህወሃት ኢህአዴግ ስርአት ላይ ቅሬታቸውን እያስሙ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቱል።