ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት ገዥው ቡድን
የሁለቱን ክልሎች ህዝብ ግጭት ለስልጣን ማራዘሚያ እየተጠቀመበት እንደሚገኝ በተደጋጋሚ በመገለፁ ምክንያት የትግራይ ክልል ርዕሰ
መስተዳደር አባይ ወልዱ ታህሳስ 23 /2007 ዓ.ም ግጭቱ ወደ ተከሰተበት ቦታ ተንቀሳቅሶ ለላይ አርማጮሆ ህዝብና ለከፍተኛ አመራሮች
ባነጋገረበት ሰዓት የሰጡት ምላሽ አንተ ችግራችንን ልትፈታልን ሳይሆን የመጣኸው ችግራችንን ልታባብስ ነው በማለት አስንስቶት ለነበረው
ሃሳብ ውድቅ እንዳደረጉት ሊታወቅ ተችሏል።
ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት አባይ ውልዱ በተመሳሳይ ዕለት ወደ ዳንሻ
በመሄድ የስርዓቱን አባላት በመሰብሰብ የግጭቱ መነሻ ምን መሆኑን በጠየቀበት ሰዓት በስብሰባው ውስጥ የነበሩት ካድሬዎች የሰጡት
መልስም በውስጣችን ሾልከው በመግባት እያጋጩን የሚገኙት የግንቦት ሰባትና
የአርበኞች አባላት ናቸው ብለው ቢመልሱም መድረኩ ላይ የተናገሩት ንግግር ግን የራሳቸው ሃሳብ ሳይሆን ወደ ስብሰባው
ከመግባታቸው በፊት በስርዓቱ ካድሬዎች እንዲናገሩት የተሰጣቸው ማደናገርያ ሃሳብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወደ ትግራይ ምዕራባዊ
ዞን አስተዳዳሪ ታህሳስ 10 / 2007 ዓ.ም በቁጥር 203/0107/በፃፈው ደብዳቤ የክልሉ ህዝብ መሬቱ ከየት ወደየት መሆኑን
እንዲያውቅ ካላደረጋችሁ በሚነሳው ጠብ ላይ የሚደርስ ጉዳት ተጠያቂዎች ራሳችሁ የትግራይ አስተዳዳሪዎች ናችሁ እንዳላቸው ከዚህ በፊት በዜና
እወጃችን መግለፃችን ይታወሳል።