Saturday, May 2, 2015

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በዓዲ ሃገራይ አካባቢ የሚገኙት የ18ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር ወታደሮች ከአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ጋር እንደተጋጩ ምንጮቻችን ገለፁ።



  ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በአዲ ሃገራይ አካባቢ የሚገኙ የ18 ሜካናይዝድ ክፍለጦር አባላት የህዝቡን ጥቅም ወደጎን ትተው የአካባቢው ህብረተሰብ ሲጠቀምበት የነበረውን ለም መሬት እራሳቸው የከባድ መሳርያ ካምፕ በማድረጋቸውና የአካባቢ ህብረተሰብ ደግሞ የእርሻ መሬታችንን ያለምንም ካሳ ተቀማን በማለት ተቃውሞ በማካሄዳቸው ምክንያት በመካከላቸው ግጭት እንደተከሰተ ለማወቅ ተችሏል።
    ነዋሪዎቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ወታደሮች ካምፓቸውን ለእርሻ በማያገግል ቦታ ላይ ይስሩ የተቀማነው ለም መሬታችን ይመለስልን በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ሃሳባቸውን ቢያቀርቡም እናንተ መኖርም ሆነ መንቀሳቀስ የምትችሉት ይህንን ሰራዊት ይዛችሁ ነው በማለት በአፈሙዝ አስፈራርተው እንደመለሷቸው የተገኘው መረጃ ገልጿል።