Saturday, May 2, 2015

ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ገለፁ።



   የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው- የምዕራብ እዝ 7ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው አስቃቂ ግፍ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት ብሎ ስለጠየቀ ብቻ ፀረ ሰላም ነህ ተብሎ ባህር ዳር መኮድ በተባለ ቦታ እንደታሰረ ምንጮቻችን አስታወቁ።
    ስርዓቱ በአይ ኤስ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ስለሌለው የዜጎቻችንን ደም መመለስ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች እንደ ጠላት እያዬ ወደ እስር ቤት እያስገባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የሚያሳዝን ተግባር ዋነኛ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ገልጿል።