Tuesday, May 5, 2015

የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር ሆነው ሲያገለገሏቸው የቆዩትን ሰዎች ህዝቡን ኢህአዴግን እንዲመርጥ በሚያስችል መንገድ አልቀሰቀሳችሁትም በማለት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው እንደሆኑ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለፀ።



በሸራሮ ከተማ የሚገኙት አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር የሚገኙትን በሃላፊነት የተቀመጡ አባላት ላይ እምነት ስላጡባቸው ነዋሪው ህዝብ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንዲመርጥ የሚያስችል አስፈላጊውን ቅስቀሳ አላደረጋችሁለትም በሚል ምክንያት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው መሆኑን የገለጸው መረጃው ከስልጣናቸው ከተወገዱት መካከልም የወረዳው ፕሮፖጋንዳ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃፍቲና የወረዳው የሴቶች ሃላፊ ወ/ሮ ደስታ ማሙ እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችሏል።
   እነዚህ በሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ ቆይተው ባሁኑ ሰአት  ከስልጣናቸው የታገዱት የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች ስርአቱ በህዝቡ ላይ ያለው ተቀባይነት ስላጣ የስርዓቱ ሃላፊዎች በነሱ ስር ለሚገኙ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸውና እየሾሟቸው አንደሆኑና ይህ ድርጊትም በሸራሮ ከተማ ብቻ ሳይሆን; በመላው ያገራችን አካባቢዎች እየተሰራበት እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።