Tuesday, May 5, 2015

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ።



የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን የማዳበርያ እዳ ቀስ ብላችሁ በሚቀጥለው አመት ትከፍሉታላችሁ በማለት በመጪው ግንቦት ወር ላይ ተመርጠው የስልጣን እድሜአቸውን ለማስረዘም ህዝቡን እያታለሉት መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
   የኢህአዴግን ተንኮል የተረዳው ህዝቡ በዚህ ተታለን እናንተን አንመረጣችሁም፤ የስልጣን እድሜያችሁን ለማስረዘም የምታደርጉት የማታለያ ቃል እንጂ ካዘናችሁልን ለምንድን ነው እዳችንን የማትሰርዙልን በማለት እንደተቃዎሟቸው ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።