በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ልዩ ቦታው መርሳ
በተባለ አካባቢ ሚያዚያ 12 /2007 ዓ.ም አቶ መሓመድ ዓሊ የተባለ ግለሰብ ምክትል ሳጅን ከበደ አበጀ ለተባለ የፖሊስ አባል
በስራው ላይ እንቅፋት ስለፈጠረበት ይዞት በነበረው ዱላ ደብድቦ እንደገደለው ከምንጮቻችን ያገኘውነው መረጃ ገለፀ።
መሃመድ አሊ ይህን የፖሊስ አባል ሊገድለው የተነሳበት ምክንያትም በአካባቢው
ነዋሪ ህዝብ ላይ የተለያዩ ግፎችን እየፈፀመ በመመልከቱ እንደሆነ የገለጸው ይህ መረጃ በተጠቀሰው ዕለትም በገበያ ላይ ስራውን እንዳያሳልጥ
እንቅፋት ስለሆነበት ገድሎት ከአካባቢው መሰወሩና መላው የአካባቢው ህብረተሰብም በዚህ ግፈኛ ፖሊስ ላይ የተወሰደውን የመግደል እርምጃ
በሰማበት ሰዓት አካባቢያችን ካሉት ጠላቶታችችን አንዱ ተወግዶልናል በማለት ደስታውን እየገለፀ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።