Thursday, May 21, 2015

በሑመራ ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ፖስተሮችን እንዳያይ ህብረተሰቡን አንድ ለአምስት በሚል ጥርነፋ መንቀሳቀሻ አሳጥውት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ሑመራ ከተማ ውስጥ ብዛት ያለው ህዝብ ለምርጫ የሚወዳደሩትን የአረና ድርጅት እጩዎች የያዘ ፖስተሮችን እያየ መሆኑን የታዘቡት የህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬዎች ስጋት ስላደረባቸው ህዝቡን አንድ ለአምስት በሚል የቡዱኑ አሰራር ማን ነው የተቃዋሚዎች ፖስተር እያየና ትኩረት እየሰጣቸው ያለው በማለት ህዝቡን እየተከታተሉት እንደሚገኙ ታውቋል።
    የህወሃት/ኢህአዴግ መሪዎች ትግራይ ውስጥ የሚወዳደሩትን ተቃዋሚ ድርጅቶች ያሸንፋሉ የሚል ስጋት ስላደረባቸው ተቃዋሚዎችን ህዝቡ እንዳያውቃቸው በሚል ፖስተራቸውን በመቅደድና ህዝቡን ከተቃዋሚዎች ጋር ተገናኝተሃል እያሉ በማስፈራራት ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።