ምንጮቻችን እንደገለፁት በትግራይ ደቡባዊ ዞን፤
አላማጣ ወረዳ፤ ጅሃን በተባለ አካባቢ የምትኖረው ወ/ሮ ፋጡማ መሓመድ የተባለችው ወገን የኢዴፓ ተቃዋሚ ድርጅት አባል በመሆኗ ብቻ
አስተዳዳሪዎቹ በጥላቻ አይን ስላዩዋት ዜጎችን ከአላማጣ እስከ ሳውዲ
አረብያ ታሸጋግሪያለሽ በሚል የሃሰት ውንጀላ ሚያዝያ 15/2007 ዓ/ም 12 ሰዓት ከምሽቱ ፌደራል ፖሊሶች ከቤቷ አስረው እንደወሰዷት
ለማወቅ ተችሏል።
ይህቺ የኢዴፓ አባል የሆነችውን ወገን ባሁኑ ግዜ በአላማጣ ፖሊስ ጣብያ
ታስራ እንደምትገኝ የገለጸው መረጃው መጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው አስመሳይ ሃገራውና ክልላዊ ምርጫ ላይ ድርጅቷን ወክላ ባካባቢው
እንድትወዳደር ህጋዊ እውቅና ተሰጥቷት እየተንቀሳቀሰች ባለችበት ወቅት ላይ ብዛት ያለው ተከታይና ደጋፊ እንዳላት ያስተዋሉት የኢህአዴግ
ብዱን አስተዳዳሪዎች ባልዋለችበት ወንጀል እየከሰሱና እያሰሩ ፈርታ ከምርጫው ራስዋ እንድታገል የተጠቀሙበት መላ መሆኑን መረጃው
አክሎ አስረድቷል።
በተመሳሳይ በደቡብ
ህዝቦች ክልል፤ ከንባታ ዞን፤ ጫጩቢራ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የኢዴፓ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት ዓላማቸውን ለህዝብ ለማስተዋወቅ ወደ
ህዝቡ በሄዱበት ግዜ ዓመፅ ለማነሳሳት ነው የምትሄዱት በሚል ምክንያት
የስርዓቱ ካድሬዎች ተላላኪዎቻቸውን በማሰማራት በማሰርና በማስፈራራት ተግባር ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አስታወቀ።
በዞኑ ውስጥ ሽሽቾ በተባለው ከተማ የኢዴፓ ድርጅት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆነውን
አቶ ደገፋ ዮናስ የተባለው ወገን የአካባቢው የኢህአዴግ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ሰዎችን እየላኩ መቃወምህን አቋርጥ እያሉት መቆየታቸውን
የገለጸው መረጃው ግለሰቡ ግን አንድ ግዜ አምኜ የገባሁበትን ዓላማ አልተወውም ስላላቸው ብቻ ሚያዝያ 16/2007 ዓ/ም ከህዝቡ ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ወንጀለኛ ነህ
በማለት ጫጩቢራ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ አስረውት እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።