Thursday, June 25, 2015

በዳንግላ ከተማ ውስጥ አንድ የአምሳ አለቃ ማእርግ ያለው የኢህአዴግ ወታደር ልጄን ደፈርካት ብሎ የከሰሰውን ሲቪል ወገን በጥይት ገድሎት መሰወሩን ተገለፀ።



    በአማራ ክልል፤ ዳንግላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የምእራብ እዝ ወታደሮች በዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀሙ መሆናቸው የገለጸው መረጃው ሃምሳ አለቃ ማሩ ፋንታሁን የተባለው ወታደር በዳንግላ ከተማ ልጄን ደፈርክብኝ ብሎ ለከሰሰው ወገን በጥይት ገድሎ ከአካባቢው መሰወሩን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
   ይህ በንዲህ እንዳለ በስርዓቱ ወታደሮች የሚፈፀመውን ሴቶችን የመድፈርና ንፁሃን ዜጎቻችንን የመግደል እርምጃ የተለመደ ተግባር ሆነ እያለ ወንጀል ለሚፈፅሙ ወታደሮች አስፈላጊውን ቅጣት መሰጠት እየተገባቸው በአዛዦቻቸው ወደ ሌላ ምድብ ተቀይረው እንዲሰሩ ስለሚደረግ ወንጀል የፈፀመው ሃምሳ አለቃም ሸሽቶ ሳይሆን ቦታው ተቀይሮ ከአካባቢው እንዲርቅ ስለተደረገ ነው በሚል ባካባቢው ህዝብ በሰፊው እየተነገረ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።