Thursday, June 25, 2015

በአማራ ክልል አብደራፊዕ ከተማ ልዩ ቦታ አዋጥር በተባለው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በስርአቱ ተላላኪዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተገለፀ።



     እነዚህ ማንነታቸው ያልታወቁት ታጣቂዎች በአውደራፊዕ ከተማ አዋጥር በተባለው አካባቢ በፀጥታ አስከባሪ ስም ስተንቀሳቀስ የነበረችውን አንድ የገዢው ስርአት የመቶ ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ላይ 3 ሲገደሉ ሌሎች 4 ደግሞ በከባድ መቁሰላቸው ምንጮቻችን ከአካባቢው የላኩልን መረጃ አመለከተ።
   መረጃው አክሎ ሰኔ 3/2007 ዓ/ም በስርአቱ ታጣቂ ሃይሎች ላይ የተወሰደው የማጥቃት እርምጃ ከቆሰሉት መካከል በርሀ ግርማይ፤ መሓሪ ደስበለ፤ ይካአሎ ገብረማሪያምና ሓጎስ ታደሰ የተባሉት ሲሆኑ ከነዚህ ውጭ ድግሞ ባተካሄደው ማጥቃት ከተበተኑት በኋላ ወደ ቦታቸው ያልተመለሱ ሰዎች አሉ በሚል በነዋሪዎች ላይ ማነጋገርያ አርእስት ሆኖ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል።