Wednesday, September 23, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አያት አደባባይ እየተባለ በሚጠራው አያት ቁጥር ሁለት ኮንዶሚኒየም አካባቢ ባልተከደነ ቱቦ ምክንያት የአንድ ሕፃን ሕይወት ማለፉ ታወቀ፣



  በአካባቢው በሚገኙት ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ በአብዛኛው የሚኖሩት በመልሶ ማልማት ከአራት ኪሎና ከተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ አደጋው የደረሰው ከእነዚህ መካከል አንዱ በሆኑት አቶ እንግዱ ዘለቀ ሕፃን ልጅ ላይ መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ/ም  እንደሆነ ሊታወቅ ተችሏል፣
የሕፃኑ ሕይወት የተቀጠፈውም የቤቶቹ ግንባታ ባለመጠናቀቁና በገዥው የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የአሰራር ግድፈት ምክንያት የተከፈቱ ቱቦዎች በመኖራቸው እንደሆነ ቤተሰቦቹ ለአንዳንድ ሚዲያዎች ገልጸዋል፡፡
 መረጃው ጨምሮም  አካባቢው ለመኖሪያነት በጣም አደገኛ እንደሆነና በየቦታው ተቆፍረው ያልተከደኑ ቱቦዎች በብዛት እንዳሉ ከገለፀ በኋላ። በጉዳዩ ላይ የአካባቢው ኅብረተሰብ መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡