Saturday, October 24, 2015

በስልጣን ላይ ያለው ገዥው የኢህአዴግ ስርአት ባለፈው አዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመቅጠር ያካሄደው የቅስቀሳ ዘመቻ ሊሳካለት ባለመቻሉ ምክንያት በድጋሜ ቅስቀሳ እያካሄደ መሆኑን ታወቀ።



      የገዥው ስርአት  ክፍለ ሰራዊቶች  ለመጠርያ ብቻ ስም  ያዙ እንጂ በውስጣቸው በሰው ሃይል እንደተመናመኑና  ለዚህም ክፍተት ለመሙላት ተብሎ ገዥው ስርአት  ካለፈው ዓመት  ጀምሮ  በርከት ያሉ ምልምል ወታደሮችን ቢያሰለጥንም ይህን ያህል ቅጥር ያለው ምልምል ሊያገኙ ስላልቻሉ ችግሮቻችው ለመፍታት ሲሉ በድጋሜ አዲስ ምልመላ ለማካሄድ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
       ባለፈው አመት በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች  አዲስ ለሚመለመሉ  ወታደሮች  የተሰጠው  ኮታ ወላጆቻቸውና ወጣቶቹ ስላልተቀበሉት ለዚህም ለማሳካት ደግሞ  ለሞያ ስልጠና በማለት ወጣቶቹን በመቀስቀስ አታልለው ወደ  ውትድርና ለማስገባት ያካሄዱት የማደናገሪያ ሙከራ  ፍላጎታቸውን ሊማላላቸው ባለመቻሉ የተነሳ አሁኑም የሙያ ስልጠና ወስደው የተባሉ ወታደሮች በመኪና ጭነው በየከተሞቹ በማዘዋወር ወጣቶቹን  እነሱን በማየት ተታልልው እንዲመዘገቡ በማድረግ ላይ  መሆናቸውን መረጃው አስታውቋል።