Monday, October 12, 2015

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ በሚያጋጥማቸው የኤለክትሪክ መቛረጥ ምክንያት ኑሮኣቸውን ለመግፋት እንደተቸገሩ ምንጮቻችን ከቦታው ዘግቦዋል።



   እንደምንጮቻችን ዘገባ መሰረት በኣማራ ክልል የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እያጋጠማቸው ባለው ተደጋጋሚ የኤለክትሪክ መቛረጥ  ምክንያት ህዝቡ በኑሮው ላይ እንቅፋት እየፈጠረበት መሆኑና በተለይ ደግሞ በብረታ ብረት፤ ብእንጨት ስራ፤ ሆቴሎችና ምግብ ቤት ከፍተው በስራ ላይ የሚገኙ የድርጅቱ ባለቤቶች በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት ላልተፈለገ ኪሳራ መጋለጣቸዉን ሊታወቅ ተችለዋል።
 ኤሌክትሪክ ቀን ጠፍቶ ከዋለ በህዋላ ለሊት ከኣምስት እስከ  ስድስት ሰዓት ጀምሮ ቢበራም ባለድርጅቶቹ መስራት የሚፈልጉትን ስራ ባለመስራታቸው ምክንያት የቤት ኪራይና  ያልሰሩበትን የመንግስትን ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸውን መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል።
እንደዚሁም ደግሞ በከተማዋ  ንጹሕ የሚጠጣ ዉሃ በመከፋፈል ላይም ችግር መኖሩንና ለዚህም ምክንያት ሊሆን የቻለው የውሃ ምንጩ በኤሌክትሪክ ሰለ ሚሰራ  ዉሃው ለነዋሪዎቹ  ስለ ማይደርስ መጉላላት እየፈጠረ መሆኑን መረጃው ጨምሮ ኣስታውቋል።