Sunday, December 6, 2015

የብሔር ብሔርሰቦች አንድነት በመጨፈር አይረጋገጥም፣



    እንደሚታወቀው ኣገራችን ኢትዮጵያ ከ 82 በላይ ብሔር ብሔርሰቦች  አቅፋ የያዘች የሰው ዘር መገኛ እንደሆነች የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋገጡት እዉነት ነው።
    በየግዚየው በሚመጡ የአገራችን መሪዎች ብሔር ብሔረሰቦች ሰብኣዊ መብታቸው ተረግጦ በህግ ፊት እኩል የማይታዩበት በቛንቛቸው ፍትህ እና ትምህርት እንደማይመለከታቸው  ተደርገው እየታዩ  አንዱ ለሌላው እየረገጠ ጥላቻ በመፍጠር የአገራችን ህዝቦች አንድነት እንዳይፈጥሩ በተለያየ ስሜት ዉስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሁኖባቸዋል።
    የተለያየ ቛንቛ  ክብርና ማንነት እንዲሁም የሚያኮራ ታሪክ ያላቸው የአገራችን ህዝቦች ወደ አንድ ጥሩ የሆነ አገራዊ ስሜት ለማምጣት ከሁሉም በፊት በቀጥታ ይሁን እምነታቸው የሰጡት ሰው አሜን ብለው የተቀበሉት ቋሚ ህገ መንግስት አላገኙም። ብቻ ሳይሆን በጥቂቶች ዉሳኔ እና እምነት የፀደቀ አብዛኛው ከቀጣይነት የገዢው ስርኣት ሁኔታ እየተተረጎመ ዴሞክራሲ እንዳይሰፍን እየተጣሰ ፍትህ እና እኩልነት የአገራችን ብሔር ብሔርስቦች  ከነበረበት በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጓል።
    አሁን በስልጣን ላይ የሚገኝ የወያኔ ኢህአዴግ ቡድን ደግሞ ከላፉት ሁለት ተከታታይ ስርአቶች ለመጥፎ ተግባሩ መሸፈኛ በህዳር 29 1987 ዓ.ም በስርአቱ አስፈፃሚ አካላት የፀደቀ ስማዊ የሆነ ህገ መንግስት ለአገራችን ብሔር ብሔረስቦች እና ህዝቦች ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ ቀጣይነት ያለው ሰላም የሚያረጋግጥ ሳይሆን በባሰ መልኩ ውስጣዊ አንድነቱ የሚሸርሸር  ሁኖ እየቀጠለ ይገኛል።
   በዚህ መሰረት ደግሞ በአገራችን የሚገኙ ብሔርስቦች  እና ህዝቦች አንድነት እንዳይፈጥሩ በስልጣን ያለ ስርአት በሚከተለው አፍራሽ የሆነ አስተዳደር በብሔሮች መካከል ቀጣይነት ባለው ግጭች እንዲነሳና  ክልላዊ ስሜት ይዘው የተለያየ የይገባኛል ጥያቄ   አንስተው የሚሰማ አካል በማጣታቸው የተነሳ በተደጋጋሚ በተቃዉሞ እየገለፁ ይገኛሉ።

    የኢህአዴግ አመራሮች በህዝብ እየተነሱ የሚገኙ የማንነትና ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው የጠየቁ ብሔር ብሔርስቦች  ጥያቄ ለመመለስ በመኮረበት ግዜ የባሰ ስሜት እንድይዙ አድርጓቸዋል።
  እንደ አብነትም በአማራ ክልል የሚገኙ የቅማንት ብሔርስቦች እያነሱት የሚገኙ ግዜ የማይሰጥ የማንነት ጥያቄ የስርአቱ አደገኛ አስተዳደር የፈጠረው ችግር ነው፣ ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጠረ የቡድኑ ስልታዊ  አስራር ስለሆነ መሰረታዊ ለዉጥ ይመጣል ብለህ መጠበቅ ከየዋህነት ያለፈ የሚያመጣው መፍትሄ አይኖርም።
    በስልጣን ላይ የሚገኝ የገዢው ስርአት ቡድን በአገር ደረጃ እየተነሳ የሚገኘው ተደጋጋሚ በህገ መንግስት የተመረኮሰ የማንነትና መብት ጥያቄዎች ለማዳከም የተፈጠረ የአሰራር ዘዴ ምክንያት የስልጣናቸው እድሜ ለማራዘም  አንዱ እንደ መደናገርያ  ከ 10 ኣመት በኋላ የብሔር ብሔርሰብቦች ቀን እያሉ በህዝብ ስም በአል በመሰየም ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ ያልተለካ ወጪ በማፍሰስ በህዝባችን ያለ እወነተኛ ሁኔታ በመዝጋት በሚዳያቸው እያደረጉ በተከታታይ 10 አመታት እየዘመሩ እና እየጨፈሩ ቆይተዋል።
   የኢህአዴግ ቡድን የአገራችን ብሔር ብሔር ሰዎች ሰላም አግኝተው ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብት ተረጋግጦላቸው በዉህደት እና በአንድነት በአገራቸው እንዲኖሩ ያደረኩኝ እኔ ነኝ ከኔ ባላይ ላሳር እያለ ሩብ ዘመን ያስቆጠረ ቢሆንም ህዝባችን ግን የስርአቱ የገዢው መደብ በሚከተለው ልዩነት የሚፈጥር አስተዳደር ለየራሱ መከባበር አጥቶ በአዋሳኝ ክልሎች በየግዝየው የሚፈጠሩ ግጭቶች መፍትሄ ያለ ማድረግ የማንነት ጥያቄ እየተነሳ ምክንያታዊ  መልስ ያለ መስጠት በሃይማኖት መካከል ጣልቃ እየገባ መበላሸት ማለት ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበርልን ብለው ለጠይቁ አካራሪዎችና የጂሃድ ጦርነት ለመካሄድ የተዘጋጁ በሚል የሃሰት ክስ በማሰርና በለሊት አፍነህ  በማጥፋት የስርኣቱ ከፍተኛ የመርገጥ መሳርያ ነው።
    በተመሳሳይ በጎረቤት ሃገራት ጠረፍ  ኪንያ ሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን መልካም ዲፕሎማሲና ሰላም የሰፈነበት ኑሮ እንዳይኖራቸው ራሳቸው በፈጠሩት መሬት ምክንያት ያለው ችግር በየግዜው እንዲነሳ እያደረጉ ቋሚ መፍትሄ እንዲያገኝ አላደረጉም።
  ሰለዚህ ብሔር ብሔረ ሰቦች በሚል ያዘጋጁት በአል ጥቂቶች ለሚድያ ሸፋን ተብለው ከየክልሉ የተወጣጡ ብሔርስቦች  አንድ አንድ ሰዎች ተወጣጥተው ስለቀረቡ የኢህአዴግ ካድሬዎና አመራሮች በመዶስኮራቸው ና በመጨፈራቸው ለአገራችን ኢትዮጵያ አንድነት  የሚገልፅ ሳይሆን እዉነቱ ሲታይ  በአንፃሩ ነው።
  ምክንያቱም ንፁኃን ወጎኖቻችን የፈፀሙት ወንጀል የሌላቸው በፊደራል ፖሊስና መደበኛ ፖሊስ እንዲሁም በወታደሮች በስርአቱ የሚሊሻ አካላት እየታደኑ በጅምላ በእስር ቤት ዉስጥ ያለ ፍርድ እየተሰቃዩ በሚገኙበት ዜጎቻችን ከጎረቤቶቻቸው ሰላም አግኝተው እንዳይኖሩ በስርአቱ ከፋፋይ አስተዳደር  ተለያይቶ ስርአቱ ህዝባዊ ግንኝነቱ ተበታትኖ በአስተያየት እና በእምነት ተለያይቶ በጥርጣሬ አይን እየታየ እንዲሄድ በተደረገበት።
  ጥሩ ፖለቲከኞች በኢህአዴግ ወጥመድ ስር ገብተው ወጎኖቻችን በስራ እጦትና በብልሹ አስተዳደር ተማርረው ወደ ስደት ሲሄዱ በተለያየ ሰሃራ በረሃና  ባህር እንዲሁም በእሳት እና በቢላዋ ህወታቸው በሚቀጠፍበት ወቕት  በኢህአዴግ ፀረ ህዝብ ስርአት የብሔር ብሔርስቦች  ቀን እየተባለ በመጨፈር ሲከበር ህዝቦቻችን የሚደሰቱበት ሳይሆን ቀኑ ራሱ የብሔር ብሔርስቦች ተብሎ መሰየሙ በጣም ያሳዝናል።
አሁንም የባለፉት  ብአላት  ቅጥያ  የብሔር ብሔርስቦች ህዝቦች ተሳትፎ ለከፍተኛ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን በሚል መርህ ቃል በስርአቱ ተሰይሞ በጋምቤላ ክልል ሲከበር ለባለፉት ተከታታይ አመታት ህዝባችን አንድነቱ ተበላሽቶ ለከፋ ተጨማሪ ችግር ተዳርጎ እያለ  በብሔር ብሔርስቦች ዉስጥ ተከስቶው በሚገኝበት ግዜ የማይሰጡ ችግሮች በመደናገር መፍታት በመጨፈር ለመግለፅ መሞከር የማይወጣ ደምነት ከማትከል አልፎ በፍፅም የአገራችን የብሔር ብሔርስቦች አንድነት አየራጋገጥም።