Friday, February 5, 2016

በጋምቤላ ክልል በአሁኑ ወቅት በተነሳው ግጭት እና ግርግር ምክንያት ህዝቡ የሚረዳው እጥቶ ወደ ጎረቤት አገሮች እየወጣ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።




       በተገኘው መረጃ መሰረት።- በጋምቤላ ክልል በአሁኑ ጊዜ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና የጠፋበት ስርአት አልበኝነት የሰፈነባት ክልል እንደሆነችና፣ የአከባቢው መሬት እየተመረጠ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለወዳጆቻቸውና ለባእድ እንቨስተሮች በመስጠት ህዝብ ተቃዉሞ እንዳያነሳ አግአዚ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ተወላጆች የሆኑ ኑዌር በማስታጠቅ በህዝባችን ላይ በመግደል እና በማስር እርምጃ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
       ገዢው የኢህአዴግ  ስርአት ለዚህ መጥፎ ተግባር መፈጸሙ የመሬት እና በክልሉ የሚካሄድ የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ መአድን ሃብት በመዉረር ወደ ዉጭ አገራት እየላኩ ኪሳቸውን እየደልቡ የነበሩ አንድዳንድ ግለሰዎች ጥቅማቸውን እንዳይጎድላቸው ሆን ብለው በአሁኑ ጊዜ የተነሳውን ግጭትና ግርግር ሆን ብለው እንዳባባሱት መረጃው አስረድተዋል።
ከዚህ ተከትሎ አኝዋክ ለቃቹ ዉጡ በማለት ለደቡብ ሱዳናዉያን ለኑዌር ታጣቂዎች መረጃ እያቀባበሉ እንዲሁም በድንበር አከባቢ ጥላቻዉን እንዲባባስና ግጭት እንዲነሳ በማድረግ በአኘዋክ መሬት ላይ የደቡብ ሱዳን ሰደተኞች የሆኑ ኑዌርን በማስፈራቸው ምክንያት  ግጭቱ  ተባብሶ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ ገልፆዋል።

No comments:

Post a Comment