Sunday, February 23, 2014

በመቐለ ከተማ በዓዲ ሓቂ አካባቢ ከሚገኙ መኖርያ ቤቶች ውስጥ የሽንት ቤት ቆሻሻዎች መንገድ ላይ እየፈሰሱ በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪዎቹ ለተለያየ በሽታዎች ተጋለጥን በማለት ብሶታቸውን እየገለፁ መሆናቸው ተገለፀ።



ይህ ከተለያዩ መኖርያ ቤቶችና ዓዲ ሓቂ አካባቢ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ የሚወጣው የሽንት ቤት ፈሳሽ ተገቢ የቆሻሻ ማስተላለፊያ ትቦ ስላልተሰራላቸውና ብዙ ህዝብ ወደ ሚገኝበት መኖርያ ቤቶች በመፍሰሳቸው ምክንያት ብዙ ህፃናቶች የሚገኝባቸው የአካባቢው ነዋሪ ለመጥፎ ጠረንና በሽታ ተጋልጠው እየተሰቃዩ መሆናቸው ከከተማው የተገኘ መረጃ አስታወቀ።
    ችግሩ እንዲፈታ በማለት በነዋሪዎቹ አማካኝነት ለሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ የቀረበው አቤቱታ ሰሚ እንዳላገኘና በተለይ የዩኒቨርሲቲ ሃላፊዎች ከተቋማቸው እየወጣ ያለው የሽንት ቤቱ ፈሳሽ በህዝቡ ላይ እያደረሰው ያለ የጤንነት ችግር እያዩ ዝምታ መምረጣቸው በህዝቡ ላይ እየደረሰ ባለው ከፍተኛ ጉዳት ተጠያቂዎች ያደርጋቸዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።