Friday, February 21, 2014

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ወታደሮች ከእድሜ በታች ለሆኑ ልጃ ገረዶች አስገድደው በመድፈር ላይ እንድሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ የሚገኙ የምዕራብ እዝ ህክምና ክፍል የመከላከያ አባላት ከእድሜ በታች ለሆኑ ሴት ህፃናት አስገድደው እየደፈርዋቸው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ይህንን ወንጀል ከሚፈፅሙት ወታደሮች መካከልም። ሓሰን ሚዐ የተባለ ወታደር መቅደስ አንተነህ ለተባለች የ12 አመት ሴት ህፃን አስገድዶ እንደደፈራትና በዚህም የተነሳ ልጅቱ አይምሮዋን ስታ በከባድ ስጋት ላይ እንደምትገኝ ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አስረድትዋል።
መረጃው ጨምሮ በዚህ ችግር ሰለባ የሆነችው ቤተሰቦች ለዚህ ሰብአዊ በደል የፈፀመ ወታደር በህግ ፊት ቀርቦ ተገቢውን ቅጣት እንዲሰጠው ላቀረቡት ጥያቄ ለግዜው ያሰሩት ቢሆንም ከሶስት ቀናት በኋላ ግን ፖሊሶቹ ከወንጀለኛው 10ሺ ብር በመቀበል የፈቱት ሲሆን ለዚህ ብልሹ የሆነ አስራር ህብረተሰቡ በመቃወም ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አስታውቁዋል።