Sunday, October 12, 2014

በአዲግራት ከተማ ለዕለታዊ ኑሯቸው የሚያስፈልጉ አላቂ ነገሮች ከገበያ በመጥፋታቸው ምክንያት ነዋሪዉ ህዝብ ምሬቱን በመግለጽ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፣



በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ከልክ ያለፈ ግብር እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ባሉበት በአሁኑ ግዜ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ንግድ-ቤታቸውን በመዝጋት ላይ እንዳሉ ታወቀ፣



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ ካድራ ከተማ ለስራ ፍለጋ ከአማራ ክልል የመጡ ወገኖቻችን በመካከላቸው በተፈጠረ ግጭት የዜጎች ህይወት እንደጠፋ ምንጮቻችን ገለጹ፣


በአማራ ክልል የሚገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ስራ ፈላጊ ለሆኑ ዜጎቻችን ወደ ትግራይ ክልል ሁመራ አካባቢ ሄደው እንዳይሰሩ መከልከላቸው ተገለፀ፣



በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች በከተማው የሚሰራውን የኮብልስቶን መንገድ ስራ ለቤተሰቦቻቸውና ጉቦ ለሚሰጧቸው ብቻ እንዲሰሩ እየፈቀዱላቸው መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣



በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ተለያዩ አገሮች የሚላኩ የኢህአዴግ ወታደሮች የሚሰጣቸው ደመወዝ ከ 35 እስከ 40 ፐርሰንት ብቻ እንደሆነና ቀሪውን ጀነራሎቹ እንደሚከፋፈሉት ተገለፀ፣