Saturday, July 4, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሰማእታት ቀን ምክንያት በማድረግ ያለፈውን ምርጫ በማንሳት ህዝቡን ሰብስበው መውቀስ በጀመሩበት ሰዓት ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።

በወልቃይት ወረዳ ተሰማርተው እየሰሩ የሚገኙት የፖሊስ ሰራዊት አባላት መሳርያቸውን ሽጠው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በብድር የወሰዱትን ገንዘብ አልወሰድንም በማለት ተመልሰው ገንዘቡን አጠፋፋኸው ብለው ለፋይናንስ ሰራተኛው ማሰራቸውን ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ውጤት ተከትሎ ቅሬታዎች በመከሰቱ ምክንያት ህዝቡ አመፅ እንዳያስነሳ ስጋት ያደረበት የኢህአዴግ ገዢ ስርአት በከተማዋ ውስጥ በርካታ ታጣቂዎች ማሰማራቱን ተገለጸ።

በኢሮብ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ባለትዳር ሴቶች በመድፈር ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ።

በአብደ ራፊዕና አብርሃ ጅራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ዜጎቻችን የአካባቢው ተወላጆች ንብረታቸውን እየቀሙ እያባረሯዋቸው እንደሚገኙ ታወቀ።

Wednesday, July 1, 2015

በአዲ-ነብርኢድ አካባቢ ከመጠን በላይ ጭና ስትጓዝ የነበረች የማእከላዊ እዝ ፓትሮል መኪና ከህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨትዋ ምክንያት ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል፤ መቱ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ድምፃችን ተሰረቀ በማለት ወደ ዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪዎች አቤቱታቸው ስላቀረቡ ብቻ በስርዓቱ ታጣቂዎች ጥይት እንደተተኮሰባቸው ተገለፀ።

ኣብ ዓብደ-ራፊዕን ኣብርሃ-ጅራን ዝርከቡ ተወለድቲ ትግራይ ዝኾኑ ወገናት ብተወለድቲ ናይ’ቲ ከባቢ ንብረቶም እናተመንጠሉ ይስጎጉን ሃለዋቶም ይጠፍኡን ከም ዘለዉ ተፈሊጡ።

ኣብ ከባቢ ዓዲ ነብርኢድ ሓንቲ ካብ ዓቐን ንላዕሊ ፅዒና ትጉዓዝ ዝነበረት ዋንነታ ናይ ማእከላይ እዚ ዝኾነት ፓትሮል ምስ ናይ ህዝቢ መማላለሲት ኣዉቶቡስ ተጋጪያ ሰለስተ ሰባት ከም ዝሞቱ ተገሊፁ።