Friday, March 16, 2018

ኣብ ኣዲስ አበባ ዝለዓለ ናይ ፀጥታ ቁፅፅር ይካየድ ከም ዘሎን ኣብታ ከተማ ካብ ቦታ ናብ ቦታ ንምንቅስቓስ ኣፀጋሚ ኮይኑ ከም ዘሎን ተሓቢሩ።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውጥረት በተሞላበት ሁኔታ መቀጠሉ ተሰማ።

በሞያሌ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በስህተት ነው በሚል በኮማንድ ፖስቱ የተሰጠውን መግለጫ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ። በሞያሌ የጦር ወንጀል ተፈጽሟል ሲልም ጠንካራ አቋም ይዟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ወራት ያለምንም በቂ ምክንያት የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ያላቸውን በርካታ የንግድ ተቋማት ቢያሽግም፣ በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር አሻቅቦ 7 ነጥብ 8 ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን የዕለት ጉርስ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተካሄደ እንደሚገኝና በከተማዋ እንደ ልብ መንቀሳቀስ አዳጋች ሆኗል፡፡