Saturday, May 23, 2015

ህዝቢ ከተማ ዉቕሮ ክልተ ኣዉላዕሎ ፅሬቱ ዘይሓለወ ማይ ክሰቲ ይግደድ ብምህላዉ ብማይ ወለድ ሕማማት ይሳቐ ከም ዘሎ ምንጭታትና ከብታ ከተማ ሓቢሮም።

ኣብ ክልል ኦሮሚያ ኣብ ከተማታት ነቀምቴን ኣረጆንን ንዝነብር ህዝቢ ካድረታት ኦህዴድ/ኢህወዴግ ናብ ሰልፊ ዉፃእ እናበሉ ዕለታዊ መነባብርኡ ከይገብር የተዓናቕፍዎ ከም ዘለዉ ተፈሊጡ።

ከተማ ኣዲስ ኣበባ ብዝተፋላለዩ ዕጡቛት ገዛኢ ስርዓት ኢህወዴግ ተኸቢባ ኣብ ከቢድ ሓለዋ ከም ዘላ ተገሊፁ።

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን ምርጫው እስኪጠናቀቅ ወደ መንገዶች እንዳይወጡ የገዥው ስርዓት ካድሬዎች ወላጆቻቸውን በማስጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 6/ 2007 ዓ/ም መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ስራ ጀመረ የተባለው የባቡር መንገድ እንዳቆመ ለማወቅ ተችሏል።

Thursday, May 21, 2015

አገራችንና ህዝባችን ማዳን አላማ አድርገን በአንድነት እንሰራለን በሚል መሪ ቃል ትህዴንን ጨምሮ አምስት የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተወያዩ መሆናቸው ተገለፀ።

የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች በሽሬና አካባቢው ለሚገኙት የህወሃት የቀድሞ ታጋዮችን ሰብስበው ድርጅታችሁን አድኑት የሚል ስብሰባ ያደረጉላቸው ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ ግን እናዳልተቀበሉት ተገለፀ።

የኢህአዴግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮነን በምእራብ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ አካባቢ ያካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳ ተቃውሞ እንዳጋጠመው ተገለፀ።

የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ለህወሃት ማጠናከሪያ የሚውል ገንዘብ እንዲያዋጣ በአስተዳዳሪዎች ቢገደድም ዛሬ ይሁን ነገ የምናወጣው ነገር የለም በማለት መቃወሙን ለማወቅ ተችሏል።


በሑመራ ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ፖስተሮችን እንዳያይ ህብረተሰቡን አንድ ለአምስት በሚል ጥርነፋ መንቀሳቀሻ አሳጥውት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።