Tuesday, August 18, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከገቢያችን ጋር የማይገናኝ ከፍተኛ ግብር ተጣለብን በማለት የንግድ ፈቃዳቸውን እየመለሱ መሆኑ ተገለፀ።

የኢህአዴግ ስርዓት ገዢ ቡድን የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን መቐለ ከተማ በሚገኘው የሰማእታት ሃውልት መሰብሰብያ አዳራሽ በጠሩት ስብሰባ ላይ ጥቂት ተማሪዎች ብቻ መገኘታቸው ተገለፀ።

የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች ችግረኞችን ለማገዝ ተብሎ ከለጋሽ ሃገሮች የሚቀርበውን የትምህርት እድል ወዳጅና ጠላት እያፈሩበት እንደሆነ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።

በቤንቺ ማጂ ዞን የሚገኙ አርሶ-አደሮች ለበርካታ አመታት ቡና በመትከል እየተጠቀሙበት የነበረውን መሬት በአስተዳዳሪዎች እየተነጠቁ መሆናቸው ተገለፀ።

በደቡብ ህዝቦች ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ያለፍላጎታቸው ማዳበሪያ እንዲገዙ በስርዓቱ እየተገደዱ በመሆናቸው ላልተፈለገ ኪሳራ እየተጋለጡ እንደሆኑ ተገለፀ።

ኣብ ዞባ ሰሜናዊ ምዕራብ ፍሉይ ሽሙ በርቀ ላፅያ ኣብ ዝተብሃለ ዶብ ከባቢ ዝርከቡ ብማጓሰ ዝናበሩ ዜጋታትና ብናይ'ቲ ስርዓት ወተሃደራዊ ሰላያ ይቕጠቐጡን ይእሰሩን ምህላዎም ተፈሊጡ።

ኣብ ዞባ ደቡብ ወሎ ወረዳ ቦረና ሳይቲ ብ4ተ ሓምለ 2007 ዓ/ም ኣብ ልዕሊ ናይ'ቲ ወረዳ ኣማሓደሪ ዝተደርበየ ናይ ኢድ ቦምቢ 2ተ ቆልዑ ከም ዝሞቱ ተገሊፁ።