Monday, September 22, 2014

ያገራችን ወጣቱ ሃይል ዋነኛው የለውጥ ሃወርያ ነው!!

መንእሰይ ሓይሊ ሃገርና ቀንዲ ናይ ለውጢ ሃወርያ’ዩ

በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ አዋልያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች የኢህአዴግ መንግስት በመጻረር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በወጡበት ግዜ በፌደራል ፖሊስና በአግአዚ ኮማንዶ መበተናቸው ተገለፀ።

በአብይ አዲ ከተማ በመንገድ ድንጋይ ምንጣፍ ስራ ላይ ተወዳድረው ለመስራት የፈለጉ በማህበር የተደራጅቱ የቀድሞ ታጋዮች በስርዓቱ እንዳይሰሩ መከልከላቸው ተገለፀ።

የአብይ አዲ እስተዳዳሪዎች በማህበር ተደራጅተው በመስራታቸው ብቻ በአይን ጥርጣሬ ሲመለከትዋቸው የነበሩትን ከ 50 በላይ የቀድሞ ታጋዮች ሲሰሩበት የቆዩትን ቦታ እንደነጠቃቸው ተገለፀ።

የዳንሻ ከተማና ያካባቢው አስተዳዳሪዎች በፅህፈት ቤታቸው ቀርበው ፍቃድ ሳይጠይቁ ወደ እርሻ መሬታቸው ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ሽፍቶች ናችሁ በማለት እያሰርዋቸው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።

የሽሬ እንዳስላሴ መብራት ሃይል ሃላፊዎች ለተገልጋዮች በማጭበርበር የማይገባቸውን ሃብት በማካበት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለጹ።

በነቀምትና ወለጋ ከተማ የሚገኙ ከዚህ በፊት ወታደሮች የነበሩ ዜጎች ለመስሪያ የሚውል ቦታ ይሰጠን ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ከአስተዳዳሪዎች ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት ምሬታቸው በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።

ኣብ ከተማ ጎንደር ዝርከቡ ናይ መበል 24 ክፍለ ሰራዊት ኣብ ከተማ ኣትዮም ኣብ ሞንጉኦም ብዝፈጥርዎ ዘለዉ ግጭት ህይወት ንፁሃት ዜጋታት ለኪሞም ይቃተሉ ብምህላዎም ነበርቲ መረረቶም ገሊፆም።

ኣብ ክልል ኣምሓራ ወረዳ ታሕታይ ኣርማጭሆ ከባቢ ኣብራሃ ጅራ ዝነብር ህዝቢ ዓመፅን ዕግርግርን ኣልዒሉ ከም ዘሎ ምንጭታትና ካብ’ቲ ከባቢ ዝለኣኽዎ ሓበሬታ ኣመልኪቱ።