Sunday, October 26, 2014

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኝ ህዝብ በጸጥታ አስከባሪዎች እየደረሰበት ያለውን ግፍ በመቃወም ፀረ ህዝብ በሆኑትን ግፈኞች ህይወታቸውን እስከ ማጥፋት እርምጃ እየወሰዱባቸው እንዳሉ ተገለጸ፣



በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ የፌደራል ፖሊስና ደህንነት አባላት በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለሚያካሂዱ ድርጅቶች የተለያየ እንቅፋት እየፈጠሩ ሊያሰሯቸው እንዳልቻሉ ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ፣



ከመቻች አዋጥር ወደ ተባለው ቦታ የሚያሻግር አንገረብ ወንዝ ላይ የሚገኙ የጉጅሌው ኢህአደግ ፌደራል ፖሊስ ሲቪሎችን ገንዘብ ለመዝረፍ ሲሉ የንፁሃን ሂይወት እያጠፉ እንዳሉ ተገለፀ፣


በበረኸት አካባቢ መሬት አርሰው ሲጠቀሙ የቆዩ ወጣቶች ባለፈው ክረምት እንደተለመደው እህል ዘርተው ጥሩ ምርት ለማፈስ ሲቃረቡ በአካባቢው አስተዳዳሪዎች እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል፣


በገዥው የኢ.ህ,አ.ዴግ ካድሬዎች በመላ ሃገራችን እየተካሄደ ያለው ተከታታይ ስብሰባ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ምንጮቻችን ከተለያዩ አከባቢዎች ገለፁ፣


የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪዎች በሃገሪቱ የተመዘገበ የመሰረተ ልማት እድገት እንደሌለ ጥቅምት 4/2007 ዓ.ም በተካሄደ ስብሰባ ላይ መግለፃቸውን ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ፣